Amharisk: ለሰፈሩ አዲስ ኖት?

To barn som sorterer avfallet i forskjellige dunker

በሪንግሳከር፣ ሐመር፣ ስታንግ እና ሎተን የከተማ መስተዳድሮች በሚኖሩበት ጊዜ ከቤት ውስጥ የሚወጣን ቆሻሻን የሚያስወግዱበት መንገድ ከዚህ በታች ተበራርቷል።

የእርስዎን ከቤት ውስጥ የሚወጣ ቆሻሻን በማስወገድ ወደ የሚተባበርዎት ሲርኩላ አይኬኤስ [Sirkula IKS] እንኳን በደህና መጡ።

እርስዎ የሚጥሉት ቆሻሻ አዳዲስ ነገሮችን ለመሥራት ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። ለዚህም ሲባል ነው እያንዳንዱን ዓይነት ቆሻሻ በመልክ በመልኩ በተቻለን መጠን ለይተን የምናስቀምጠው። ለምሳሌ፣ ጥቅም ላይ የዋሉ ወረቀት ነክ ነገሮች ወደ አዲስ የወረቀት ዕቃዎች፣ የጠርሙስ ጣሳዎች ወደ አዳዲስ ጣሳዎች እና የቆርቆሮ ጣሳዎች ወደ አዳዲስ ጣሳዎች ወይም ለምሳሌ ወደ ብስክሌትነት ሊለወጡ ይችላሉ።

በእኛ የምንጥለው ቆሻሻ ውስጥ ያሉትን መሠረታዊ ቁሳቁሶች ዳግም ጥቅም ላይ ማዋል ለእኛ ለራሳችን እና ለመጻኢ ትውልዶች ለሁለታችንም ከምድር የሚገኙ የተፈጥሮ ሃብቶችን ተገኝነት ብዛት መጨመር እንድንችል ያግዘናል።

በሪንግሳከር፣ ሐመር፣ ስታንግ እና ሎተን የከተማ መስተዳድሮች የሚገኙ ሁሉም መኖሪያ ቤቶች ተመሳሳይ የሆነ የቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓትን የሚጠቀሙ ሲሆን ይህንንም ሲርኩላ [Sirkula] በበላይነት ይመራዋል። እያንዳንዱ መኖሪያ ቤት ለዚህ አገልግሎት ቆሻሻ ለሚሰበሰብበት ዓመታዊ  የአገልግሎት ክፍያን ይከፍላል። በዚህ አገልግሎት ሥር የሚካተቱ አገልግሎቶች፦

የመኖሪያ ቤት ቆሻሻን መሰብሰብ

ከእርስዎ መኖሪያ ቤት አምስት ዓይነት የቤት ውስጥ ቆሻሻዎች ይሰበሳባሉ፦ የምግብ ትራፊ፣ ፕላስቲክ፣ ወረቀት፣ ምንም ዓይነት ጥቅም ላይ ሊውሉ የማይችሉ ቆሻሻዎች ጠርሙስ እና ብረት ነክ እሽጎች።

ለእነዚህ እያንዳንዳቸው የየራሳቸው የቆሻሻ መጣያ ዕቃ በግቢዎ ውስጥ ይኖርዎታል። እነዚህ ቆሻሻ መጣያ ዕቃዎች የሲርኩላ ንብረቶች ሲሆኑ አስፈላጊውን ክትትል ይኸው ድርጅት ያደርግላቸዋል፤ ዕቃዎቹ እርስዎ በሚኖሩበት ግቢ ውስጥ ሁልጊዜ መቀመጥ ይኖርባቸዋል። በጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ፣ በአፓርታማ ብሎክ ወይም ተመሳሳይ ቤቶች የሚኖሩ ከሆነ የጋራ የሆኑ የቆሻሻ መጣያዎችን ከሌሎች ነዋሪዎች ጋር ሊጋሩ ይችሉ ይሆናል።

ደረጃቸውን የጠበቁ የቆሻሻ መጣያዎች እንደ የሚጣልባቸው ዓይነት ቆሻሻ የተለያየ ቀለም ያለው መክደኛ አላቸው። ከዚህ በተጨማሪ ለፕላስቲክ ቆሻሻ መሰብሰቢያ የሚሆን ለብቻው የተለየ ውስጡ ምን እንዳለ የሚያሳይ የፕላስቲክ ከረጢት ይኖርዎታል።

 Avfallsbeholder for papir, matavfall, restavfall, glass- og metallemballasje og plastsekk for plast

አራት ቆሻሻ መጣያ በርሜሎች እና አንድ ውስጡ የሚያሳይ የፕላስቲክ ቆሻሻን ለመሰብሰብ የሚያገለግል የፕላስቲክ ከረጢት እያንዳንዱ መኖሪያ ቤት በመደበኛነት የሚኖሩት የተመደቡለት የቆሻሻ መጣያዎች ናቸው።

Renovatør som tømmer papir- og matavfallsdunker i to-kamret renovasjonsbil

የቆሻሻ መጣያ በርሜሉ እና ውስጡ የሚያሳየው የፕላስቲክ ከረጢት በተለያዩ እኩል ጊዜያት ልዩነት ይሰበሰባሉ፦

 

  • የምግብ ትራፊ (ቡናማ መክደኛ) በየ 2 ሳምንቱ ይጸዳል።
  • ፕላስቲክ (ውስጡ የሚያሳይ የፕላስቲክ ከረጢት)፣ ወረቀት (ሰማያዊ መክደኛ) እና ተመልሰው ምንም ጥቅም ላይ የማይውሉ ነገሮች (ግራጫ መክደኛ) በየ 4 ሳምንቱ ይጸዳሉ።
  • ብርጭቆ እና የብረት እሽጎች የመሳሰሉ ቆሻሻዎች በየ 8 ሳምንቱ ይሰበሰባሉ።

ለበለጠ መረጃ Tømmekalender (የቆሻሻ አሰባሰብ ቀን መቁጠሪያ) የሚለውን ይመልከቱ - በየትኛው የሳምንቱ ቀን የቆሻሻ መጣያ በርሜሎቹ እንደሚጸዱ ለማወቅ www.sirkula.no - ን ይመልከቱ።

የቆሻሻ መጣያ በርሜሎች/የፕላስቲክ ከረጢቱ ቆሻሻው ከሚሰበሰብበት ቀን ቀደም ብሎ ባለው ምሽት ላይ ለመሰብሰብ እንዲመቹ ተደርገው ከቤት ውጭ ዝግጁ ሆነው መቀመጥ አለባቸው።

Brun plastpose til matavfall og en rull med slike poser

የምግብ ትራፊ ወደ በርሜሉ ከመቀመጡ በፊት ራሱ በራሱ በሚበሰብስ ልዩ ቡናማ ከረጢት ውስጥ ይቀመጣል። ወደ በርሜሉ ውስጥ ከማስቀመጥዎ በፊት ከረጢቱን በሚገባ እንዳይፈስ አድርገው እንደቋጠሩት ያረጋግጡ።

ለምግብ ወይም ለፕላስቲክ ቆሻሻ እንዴት አዲስ ከረጢቶችን ማግኘት እንደሚቻል

Handlepose knyttet på håndtak restavfallsbeholder og brun matavfallspose knyttet på håndtak til matavfallsdunk

ለፕላስቲክ ቆሻሻ ጥቅም ላይ የሚውለው ውስጡ የሚያሳየውን የፕላስቲክ ከረጢት ሲያልቅብዎት ምንም ነገር የሌለበት ባዶ ዝርግ የፕላስቲክ ከረጢት (ከሱፐር ማርኬት የሚሰጠው ከረጢትን ወይም ሌላ ዓይነት የፕላስቲክ ከረጢት) ቆሻሻ ከመሰብሰቡ በፊት በቆሻሻ በርሜሉ ላይ በመቋጠር አዲስ የከረጢት ጥቅልን ማግኘት ይችላሉ።  የእርስዎ ቆሻሻ በሚወሰድበት ጊዜ በዚህ መልኩ አዲስ የከረጢቶች ጥቅል ይሰጥዎታል። አዲስ የፕላስቲክ ከረጢቶች ጥቅል ልክ እንዳገኙ ከቆሻሻ መጣያ በርሜሉ ላይ የቋጠሩትን ባዶ የፕላስቲክ ከረጢት ማስወገድ እንዳለብዎት አይዘንጉ።

ቡናማው የምግብ ትራፊ ማጠራቀሚያ የቆሻሻ ከረጢት ሲያልቅብዎት ቆሻሻ ከሚሰበሰብበት ቀን ቀደም ብሎ ቡናማ የምግብ ትራፊ ከረጢትን በቆሻሻ መጣያ በርሜሉ ላይ በመቋጠር አዲስ ከረጢቶችን ማግኘት ይችላሉ። የእርስዎ ቆሻሻ በሚወሰድበት ጊዜ በዚህ መልኩ አዲስ የከረጢቶች ጥቅል ይሰጥዎታል።

ከዚህ በተጨማሪ አዳዲስ የፕላስቲክ ቆሻሻ መጣያ ከረጢቶችን እና የምግብ ትራፊ መሰብሰቢያ ከረጢቶችን በዳግም አድሶ መጠቀሚያ ጣቢያዎች፣ ከማዘጋጃ ቤት አገልግሎት ቢሮ ማግኘት ይችላሉ።

ቆሻሻን ወደ መልሶ ማደሻ ማእከላት ራስ ወስዶ ማድረስ

Gjenvinningsstasjonen i Brumunddal sett fra inngangsparti

ከምግብ ትራፊ በስተቀር ሁሉንም ዓይነት ቆሻሻ በሥራ ሰዓታት በሰው ወደ የሚንቀሳቀሱት የመልሶ ማደሻ ማእከላት ራስዎ ወስደው ማድረግ ይችላሉ። በተለይ ለሕዝብ ጤና እና ለከባቢያዊ አየር አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ ነገሮችን አደጋ ከማድረሳቸው በፊት መከላከል እንዲቻል መርዛማነት ያላቸውን ቆሻሻ ቁሳቁሶች ወደ ዳግም ማደሻ ማእከላት ራስዎ አምጥተው ማስረከብዎ እጅግ አስፈላጊ ነው። መርዛማ ቆሻሻ ሲባል እንደ ባትሪዎች፣ የመብራት አምፖሎች፣ ቀለም፣ የጋዝ ቆርቆሮዎች፣ ዘይት፣ ጸረ-ተባይ መርዞች እና የአረም ማጥፊያዎች፣ የሞባይል ስልኮች፣ የኤሌክትሪክ ሽቦ ገመዶች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና ሌሎች ኤሌክትሪክ የሚጠቀሙ ምርቶችን ማለታችን ነው።

Bilde av rød beholder for farlig avfall

መርዛማ ቆሻሻ ለመጣል፡ ቀዩን ፌስታል ይጠቀሙ።


ከምግብ ትራፊ በቀር ወደ ዳግም ማደሻ ማእከላት የግል የሆነን የቤት ቆሻሻን ወስዶ በማስረከብ ምክንያት የሚከፈል ምንም ዓይነት ተጨማሪ ክፍያ የለም። sirkula.no ገብተህ ክፍያውን መመልከት ይችላሉ።


በዳግም አድሶ መጠቀሚያ ጣቢያዎች፣ ተመልሰው ምንም ጥቅም ላይ የማይውሉ ነገሮች ለመጣል ውስጡ የሚያሳይ የፕላስቲክ ከረጢት ይጠቀሙ። እነዚህ የፕላስቲክ ከረጢቶች፡ ከሱፐር ማርኬት ወይ ከሲርኩላ መግዛት ይችላሉ።

የዳግም ማደሻ ማእከላት የጎዳና አድራሻ፦

በሚከተለው አድራሻ ላይ የዳግም ማደሻ ማእከላቱን የሥራ ሰዓታት ማግኘት ይችላሉ፦  www.sirkula.no

የእርስዎን የቤት ቆሻሻ በመልክ በመልኩ ስላስቀመጡ እናመሰግናለን!

ቆሻሻንበመልክበመልኩማስቀመጥንበተመለከተእገዛማግኘትከፈለጉ፦  www.sirkula.noይጎብኙ

ለ የሚያገለግልዎት ቆሻሻን በመልክ በመልኩ የመለያ ዘዴ መመሪያ ከዚህ በታች ተሰጥቷል

ቆሻሻ የሚሰበሰብባቸውን ቀናት መተግበሪያውን በእርስዎ ስልክ ላይ በማውረድ (ዳውንሎድ በማድረግ) አስቀድመው ማስታወሻ የጽሑፍ መልእክት በስልክዎ ላይ ያግኙ፦ Min Renovasjon (IOS - Android)

Sirkula IKS

አድራሻ፦ P.O Box 3, 2301  Hamar

ስልክ ቁጥር፦ 62 54 37 00

ኢሜይል፦ Post@sirkula.no

ድረ-ገጽ፦ www.sirkula.no

Fant du det du lette etter?

Takk for din tilbakemelding

Vi vil bruke din og andres tilbakemelding for å kontinuerlig forbedre denne siden.

Hva forsøkte du å finne?